የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት የጋራ መኖሪያ ቤት እየገነባ ነው። 

27

ጎንደር: ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚኾን የጋራ መኖሪያ ቤት እያስገነባ መኾኑን አስታውቋል። የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ በከተማዋ በርካታ መሠረተ ልማቶች እየተሠሩ እንደኾነ ተናግረዋል። እየተከናወኑ ከሚገኙ የልማት ሥራዎች መካከል የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ አንዱ ነው ብለዋል።

‎የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታው ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሚደረግበት ሲኾን በአራት ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።

‎ግንባታው በ1 ሺህ 300 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ባለ አራት ወለል ሕንጻ ነው። ሲጠናቀቅም በእያንዳንዱ ወለል ላይ 30 አባዎራዎችን እንደሚይዝ ነው ምክትል ከንቲባዋ የገለጹት። ‎ግንባታው በከተማ አሥተዳደሩ እና በከተማዋ ካሉ ባለሀብቶች በተገኘ ገንዘብ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑንም ተናግረዋል።

ግንባታው በከተማዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር የሚያቃልል እና አቅም የሌላቸው ዜጎችን የቤት ባለቤት የሚያደርግ ስለመኾኑም አስታውቀዋል ።

‎የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሙሉጌታ ታደሰ

ግንባታውን በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

‎ዘጋቢ፦ ማህደር አድማሴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየባሕር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማዋን የተፈጥሮ ውበት ይበልጥ የሚያጎላ ነው።
Next articleማኅበራዊ ሚዲያ እና ጤና