በጽንፈኛ ቡድኑ ተይዞ የነበረን የውኃ ማውጫ ማሽን ማስመለሱን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ። 

81

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጽንፈኛ ቡድኑ ተይዞ የነበረን የውኃ ማውጫ ማሽን ማስመለሱን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት በ304ኛ ኮር የ79ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ገብረ ኪዳን ሀድጉ ጽንፈኛ ቡድኑ በአማራ ሕዝብ ላይ በደል እያደረሰ መኾኑን ገልጸዋል።

ጽንፈኛ ቡድኑ የሕዝብ ሃብትና ንብረት እንደሚዘርፍም ተናግረዋል። ጽንፈኛ ቡድኑ በጭንባ ደና ማርያም አካባቢ የውኃ መውጫ ማሽኖች በማገት በከፍተኛ ገንዘብ ሲደራደርባቸው እንደነበርም ገልጸዋል።

መኪናዎቹ የጭስ እሳት ውኃ ሥራዎች ድርጅት እንደኾኑም ተናግረዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት በአካባቢው ባደረገው ኦፕሬሽን ማስለቀቅ መቻሉንም ገልጸዋል። ጽንፈኛ ቡድኑ የማሽኖችን አሽከሪካሪዎች እና ተሽካርካሪዎችን ለየብቻ ገንዘብ ተምኖ በሚሊዮን በሚቆጠር ብር ሲደራደርባቸው እንደነበርም አንስተዋል።

ማሽኖቹ ለሕዝብ ልማት ነው የሚሠሩት ያሉት ኮሎኔሉ ከሕዝብ ልማት ውጭ ሌላ የሚሠሩት ሥራ እና ተልዕኮ እንደሌላቸውም ገልጸዋል። ሠራዊቱ ማሽኖችን አስመልሶ ለባለቤቱ ማስረከቡንም ተናግረዋል።

መከላከያ ሠራዊቱ ማሽኖችን አግቶ የነበረውን ኃይል በመደምሰስ እንዳስመለሰም ገልጸዋል። ጀግናው የሀገር መከላከያ የሠራው ሥራ የሚያስደንቅ መኾኑንም አንስተዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት በየትኛውም አካባቢ በሚገኝን ጽንፈኛ እና ጸረ ሕዝብ ኃይል ላይ እምርጃ እንደሚወስድም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከግጭቱ ወጥታ ወደ ተሻለ ልማት እና ዕድገት እንድትሄድ እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል። በግጭት የሚገኙ ኃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ለሰላም መግባት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። የሚሻለው ሰላም እና ልማት መኾኑንም ተናግረዋል።

በኃይል የሚደረግ እንቅስቃሴ ግን ተቀባይነት እንደሌለው እና የማይቻል መኾኑንም ገልጸዋል። አዋጩ ሰላም እና ድርድር እንደኾንም ተናግረዋል። ኅብረተሰቡ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እየሰጠው ያለው ድጋፍ ከፍተኛ መኾኑንም ገልጸዋል።

አሁንም ይህን ጸረ ሰላም ኃይል አንፈልግህም ማለት እንደሚገባውም ተናግረዋል። ማኅበረሰብን እያሰቃየ፣ ልጆቹን እያገተ፣ ንብረቱን እየዘረፈ መኖር በቃህ ሊባል ይገባል ነው ያሉት።

ማኅበረሰቡ እያደረገው ላለው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጎንደር ዩኒቨርሲቲ የገዘፈ እና የላቀ ኾኗል። 
Next articleየተሰጣቸው ሥልጠና ለሚሠሩት ተግባር ተጨማሪ አቅም እንደፈጠረላቸው ሴት መሪዎች ተናገሩ፡፡