በ171 ወረዳዎች የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አሥተዳደር ሥርዓት ተግባራዊ ተደርጓል።

9

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የግብር አሠባሠብ ሥርዓቱን ለማዘመን እየሠራ እንደሚገኝ በቢሮው የግብር ትምህርት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ታዘባቸው ጣሴ ገልጸዋል።

የግብር አሠባሠብ ሥርዓቱን ከተለምዷዊ አሠራር ለማውጣት የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አሥተዳደር ሥርዓት (ኢ-ታስ) ተግባራዊ መደረጉን ገልጸዋል። የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አሥተዳደር ሥርዓት ግብር ከፋዩ ባለበት ኾኖ በዲጂታል መንገድ ግብርን የሚከፍልበት ሥርዓት ነው።

ዳይሬክተሩ እንደገለጹት አሠራሩ ከሐምሌ/2017 ጀምሮ በ171 ወረዳዎች በሚገኙ የደረጃ “ሐ” እና የኪራይ ግብር ከፋዮች ላይ ተግባራዊ ተደርጓል።
በቀጣይ በሌሎች ግብር ከፋዮች ላይም የሚተገበር ይኾናል።

ኢ-ታስ በጀመረባቸው አካባቢዎች የገቢ ሠራተኞችን እና የግብር ከፋዮችን ግንኙነት፣ ረጅም ሰልፎችን እና ወረፋዎችን በመቅረፍ ይባክን የነበረውን ጊዜ፣ ሀብት እና ጉልበት አሥቀርቷል ነው የተባለው።

ፍትሐዊነት እና ሚዛናዊነትን ማስፈንም ተችሏል። ለሕግ ተገዥ ያልኾኑ ግብር ከፋዮች ወደ ግብር መረቡ እንዲገቡም ተደርጓል ነው ያሉት። የወረቀት ሥራንም አሥቀርቷል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleከዘመናዊነት ጋር እየተፈተነ ያለው ጡት የማጥባት ተግባር በትኩረት ሊሠራበት ይገባል።
Next articleየክረምት በጎ ፈቃድ በጎነትን አጉልተን የምናሳይበት ነው፡፡