የዲጅታል ግብር አሠባሠብ ሂደት ተግባራዊ እየኾነ ነው።

14

ባሕር ዳር: ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎‎ለግብር አሰባሰብ ሥርዓቱ ልዩ ትኩረት በመስጠት ገቢ እየተሰበሰበ መኾኑን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል። የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ግብር ትምህርት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ታዘባቸው ጣሴ በአማራ ክልል ከ467 ሺህ 330 የደረጃ “ሐ” እና የኪራይ ግብር ከፋዮች ግብር የመሰብሰብ ሥራ እንደተከናወነ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ እንደገለጹት የግብር አሠባሰብ ሂደቱ በተለመደው መንገድ (በማኑዋል) እና በዲጅታል መንገድ እየተካሄደ ይገኛል ነው ያሉት።

በዚህም በተለመደው መንገድ ግብር ለመሰብሰብ ከታቀደው 353 ሺህ 190 የደረጃ “ሐ”ግብር ከፋዮች ውስጥ እስከ ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም ድረስ 41 ነጥብ 4 በመቶ የሚኾኑት ከፍለዋል ብለዋል።

በማኑዋል ለመሰብሰብ ከታቀደው ከ114 ሺህ 140 የመኖሪያ እና የድርጅት ኪራይ ግብር ከፋዮች ውስጥ ደግሞ 24 ነጥብ 7 በመቶ የሚኾኑት ከፍለዋል ነው ያሉት።

ዳይሬክተሩ ከተለመደው የግብር አከፋፈል ባለፈ ከሐምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ የዲጅታል ግብር አሰባሰብ ተግባራዊ ኾኗል ብለዋል።

በዲጅታል ግብር ለመክፈል ከተመዘገቡ 126 ሺህ 623 ግብር ከፋዮች ውስጥ 90 ሺህ 424 ውሳኔ ተሰጥቷቸዋል ነው ያሉት።

ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ፣ ወልድያ እና ደብረ ታቦር ከተሞች እንዲሁም ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች በዲጅታል አከፋፈል የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው እንደኾኑም ጠቁመዋል።

በቀጣይ የግብ አከፋፈል ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ በዲጅታል መንገድ ለማከናወን እየተሠራ መኾኑንም ነው የገለጹት።

ዘጋቢ: ዳግማዊ ተሠራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበኅብረተሰቡ ውስጥ የተከሰቱ የጤና ችግሮች ላይ ውጤታማ ሥራ ተሠርቷል፡፡
Next articleከዘመናዊነት ጋር እየተፈተነ ያለው ጡት የማጥባት ተግባር በትኩረት ሊሠራበት ይገባል።