የዓለም የጡት ማጥባት ሳምንት በክልል ደረጃ እየተከበረ ነው።

33

ባሕር ዳር: ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የዓለም የጡት ማጥባት ሳምንትን በክልል ደረጃ እያከበረ ነው። ቢሮው የጡት ማጥባት ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የመርሐ ግብሩ አንዱ አካል የኾነ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የዞን እና የከተማ አሥተዳደሮች የጤና መምሪያ ኀላፊዎች፣ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የውይይት መርሐ ግብር ጡት ማጥባት ለሕጻናት ሁለንተናዊ ጤንነት ያለውን ፋይዳ በተመለከተ ግንዛቤ የሚፈጥሩ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ነው።

ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleተከስተው የነበሩ የኅብረተሰብ ጤና ችግሮችን በቅንጅት በመሥራት መቆጣጠር ተችሏል። ‎
Next articleየሴፍትኔት ፕሮግራም ዜጎችን ከተረጅነት ወደ አምራችነት እያሸጋገረ ነው።