
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም አሥተዳደር ዞን በመርዓዊ ከተማ የተገነቡትን እና እድሳት የተደረገላቸውን ቢሮዎች እና የአገልግሎት መስጫ ተቋም እየተመረቁ ነው።
ከሚመረቁ ልማቶች ውስጥ የከተማ አሥተዳደሩ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት፣ የፖሊስ ጽሕፈት ቤት፣ የብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ መናኸሪያ አገልግሎት ይገኝበታል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በምሥራቅ ዕዝ የ304ኛ ኮር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዲሱ መሐመድ፣ የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሰፋ ጥላሁን፣ የሰሜን ጎጃም ዞን ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ማስተዋል አሰሙ እና ሌሎችም ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን