ከ44 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።

9

ደብረ ማርቆስ: ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ክፍለ ከተማ በማኅበረሰቡ ተሳትፎ እና በመንግሥት የተገነቡ ስምንት ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።

በክፍለ ከተማው የመንገድ፣ የመብራት፣ የጥቃቅንና አነስተኛ የሥራ ዕድል ማሠልጠኛ ማዕከል እና ሌሎችም ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ተመርቀዋል።

የንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ክፍለ ከተማ የከተማና መሠረተ ልማት ሥራ አስኪያጅ ዮሐንስ ክቡር የተሠሩ መሠረተ ልማቶች በመንግሥት እና በማኅበረሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ከ44 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው መኾናቸውን ተናግረዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች የተሠሩ የልማት ሥራዎች ጥያቄዎች የመለሱ መኾናቸውን ጠቅሰው የልማት ሥራዎቹ የታለመላቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ እንጠብቃቸዋለን ብለዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ መንግሥት ከማኅበረሰቡ ጋር በቅንጂት ሰላምን ለማስፈን ከሚሠራው ሥራ ጎን ለጎን ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

በክፍለ ከተማው የተመረቁ ፕሮጀክቶች በከተማው ለሚገኙ ሌሎች ክፍለ ከተሞች በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ ነውም ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ ለምርቃት እንዲበቁ ድጋፍ ላደረጉ የተለያዩ አካላት እውቅና ተሰጥቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደረገ።
Next articleየጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሰው ተኮር ተግባራትን እያከናወነ ነው።