በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደረገ።

24

ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ግምቱ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል።

ለተፈናቃዮች ድጋፉን ያደረጉት የሸዋ ሰላምና ልማት ማኅበር ከግሎባል አሊያንስ ከጀርመን ሙኒክ ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያውን ጋር በመተባበር ነው።

በከተማው በተለምዶ በቻይና፣ በወይንሸት እና በባቄሎ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ 2 ሺህ አባወራዎች ነው ድጋፍ የተደረገው።

የሸዋ ሰላምና ልማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሠማ ተፈናቃዮች ካሉባቸው ውስብስብ ችግሮች አንጻር የተደረገው ድጋፍ በቂ ባይኾንም በተወሰነ መልኩ ችግራቸውን እንደሚፈታ ተናግረዋል። ተፈናቃዮችን በቋሚነት ማቋቋም ላይም በትኩረት ሊሠራ ይገባል ነው ያሉት።

ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ ልብ ሰባሪ መኾኑን ያነሱት ደግሞ የግሎባል አሊያንስ በኢትዮጵያ ማኅበር ተወካይ በፍቃዱ ዓባይ ናቸው። ማኅበሩ ከበጎ ፈቃደኞች በማሰባሰብ በቀጣይ ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።
የክረምቱ ዝናብ እና ቅዝቃዜ ለከፍተኛ ችግር እንዳጋለጣቸው ተፈናቃዮች ተናግረዋል።

ለተደረገልን ድጋፍ እናመሰግናለን ያሉት ተፈናቃዮች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶችም መሰል ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ዘጋቢ:- ብርቱካን ማሞ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበመርዓዊ ከተማ ሰው ተኮር የመሠረተ ልማት ሥራዎች ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።
Next articleከ44 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።