
ደብረታቦር፡ ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በጤናው ዘርፍ ያሠለጠናቸውን 121 ተማሪዎች አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ ውስጥ 42ቱ ሴቶች ናቸው።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ፕሬዝዳንት ሀብቱ ወርቁ (ዶ.ር) የጤና ሙያ ከፍተኛ ዕወቀትን፣ ቀና አመለካከትን እና ሰብዓዊነትን የሚጠይቅ መኾኑን ተናግረዋል።
ተመራቂ ተማሪዎችም በቆይታቸው ያዳበሩትን ልምድ በተግባር እንዲያሳዩም አደራ ብለዋል።
“በምትሰማሩበት የሙያ መስክ ዕውቀትን፣ ችሎታን እና ሰብዓዊነትን በመላበስ በገባችሁት ቃል ኪዳን መሠረት ሕዝባችሁን በታማኝነት እንድታገለግሉ” ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
አሚኮ ያነጋገራቸው ተመራቂ ተማሪዎችም በተማሩት የሙያ መስክ ማኅበረሰቡን እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል። የጤና ሙያ የሕሊና ሥራ ነው፣ ማስተዋልን እና ቅድሚያ ለሰው ማሰብን የሚፈልግ ነው ብለዋል።
ሙያዊ ሥነ ምግባርን በመላበስ ለማገልገል ቁርጠኛ መኾናቸውንም ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን