
ባሕርዳር ፡ ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በምክክር ሂደቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ዕውቅና ሰጥቷል።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዓላማዎች እና ግቦች እንዲሳኩ፣ በኢትዮጵያ ችግሮችን በምክክር መፍታት ባሕል እንዲሆን በትኩረት ሠርቷል። እየሠራም ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢ አጀንዳዎችን ሲያሰባስብ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲመካከር እና በሌሎች ሥራዎቹ ሁሉ ግንባር ቀደም ኾኖ ሠርቷል።
አሚኮ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚሠራቸው ሥራዎች ኢትዮጵያውያን በቋንቋቸው እንዲሰሙት በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽ ኾኗል። ለአድማጮች፣ ለተመልካቾች እና ለአንባቢያን በቋንቋቸው ቀርቦ ሠርቷል።
አሚኮ የምልክት ቀንቋን ጨምሮ በ12 የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቋንቋዎች ትልቅ አበርክቶ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም ዛሬ ባካሔደው የእውቅና ሥነ ሥርዓት አሚኮ ባለፉት ሦሥት ዓመታት ከአራት ወራት የኮምሽኑን ሥራዎች በማገዝ ላበረከተው አስተዋጽዖ ነው ዕውቅና የሰጠው።
አሚኮ በዋናው መሥሪያ ቤት እና በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለሀገራዊ ምክክሩ ላበረከው አስተዋጽዖ ሁለት የዕውቅና ሰርተፍኬት ነው የተበረከተለት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን