በኮሪደር ልማት ሥራ የወልድያ ከተማ ገጽታ እየተቀየረ ነው።

14

ወልድያ፡ ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ገጽታዋ እየተለወጠች ያለችው ወልድያ ከተማ በኮሪደር ልማት ሥራ ውበቷ መታየት ጀምሯል።

ለአሚኮ ሃሳባቸውን ያካፈሉ የከተማዋ ነዋሪዎች በከተማቸው እየተከናወኑ በሚገኙ ፈጣን እና ተጨባጭ የልማት ሥራዎች ደስተኞች መኾናቸውን ገልጸዋል።

ከተማዋ እንደ ጥንታዊነቷ በሚገባት ልክ አለመልማቷን ያነሱት ነዋሪዎቹ የኮሪደር ልማት ሥራውን ተከትሎ ወልድያ ከተማ እንደ አዲስ ተወልዳለች ነው ያሉት።

በቀጣይም በነቃ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ የኮሪደር ልማት ሥራውን በከተማዋ በተሻለ አፈፃፀም ማስቀጠል ያስፈልጋልም ብለዋል።

ለነዋሪዎች ምቹ ያልኾኑ አካባቢዎች፣ የተጣበቡ የመኪና እና የግረኛ መንገዶች በጥራት እየተሠሩ መኾኑንም ተናግረዋል። በልማት ሥራውም የወልድያ ከተማ ሕዝብ ደስተኛ መኾኑን ገልጸዋል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ በከተማዋ በመሠራት ላይ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ በከተማ አሥተዳደሩ አቅም የሚከናወን መኾኑን ተናግረው በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እየተከናወነ መኾኑን አንስተዋል።

“በኮሪደር ልማት ሥራ የወልድያ ከተማ ገጽታ እየተቀየረ ነው” ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ከተማዋን ውብ፣ ጽዱ፣ ምቹ እና የቱሪዝም ማዕከል እንድትኾን በትኩረት እየተሠራ ያለው ሥራ ውጤታማ ነው ብለዋል።

ለለውጡ የከተማው ነዋሪዎች እገዛ የላቀ መኾኑን ያነሱት አቶ ዱባለ አብራሬ በከተማዋ እየተከናወኑ ባሉ ሁሉን አቀፍ የልማት ሥራዎች ደስተኞች መኾናቸውንም አንስተዋል።

ዘጋቢ፦ አበሻ አንለይ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበደብረ ብርሃን ከተማ ከ7 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በስንዴ ዘር ይሸፈናል።
Next articleካለን እናካፍል።