የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

48

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼክ ሀሰን የበሬ ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል የለውጥ ስራዎችን ጎብኝተናል።

ሆስፒታሉ ከለውጡ በፊት ታካሚዎችን ለእንግልት ሲዳርግ የቆየውን የአገልግሎት አሰጣጥ በመሰረታዊነት የቀየረ ሥራዎችን አሁን እውን አድርጓል። በተለይ ለታካሚዎች የሚሰጠውን አገልግሎት የሚያዘምኑ የጤና መሠረተ ልማቶችን በማሟላት ሰፊ አገልግሎትን እየሰጠ እንደሚገኝም ተመልክተናል።

ሆስፒታሉ የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችና ዘመናዊ የህክምና ቁሳቁሶችን በሟሟላት ለተጠቃሚው የህብረተሰብ ክፍል ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ሰፊ የአገልግሎት ማሻሻያና የማስፋፊያ ሥራዎችን አከናውኗል።

የሆስፒታሉ አረንጓዴ ምድረ ግቢ ለህክምና አገልግሎት የሚመችና ፅዱ የሥራ ከባቢ እንዲፈጠር አድርጓል።
በሌላ በኩል በጅግጅጋ ከተማ ሁሉን አቀፍ እንዲሁም ዘመኑን የዋጀ የተቋም ግንባታን እያከናወኑ የሚገኙትን የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ ቤትን አይተናል፡፡

ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂና በቢሮ እድሳት አስደናቂ ለውጥ ላይ እንደሚገኙም ተመልክተናል፡፡

Previous articleሀገርን የሚቀይሩ የምርምር ውጤቶችን ማን ይተግብራቸው ?
Next articleባሕር ዳር ከተማ ለመግባት የተቃረበችው ጣናነሽ ፪ ለከተማዋ ቱሪዝም ተደማሪ አቅም ናት።