
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 13ኛው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የፌዴራል እና የክልል ባለድርሻ የመንግሥት ተቋማት የጋራ ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዘላቂ እና የላቀ አስተዋጽኦ ለሀገራዊ ማንሠራራት በሚል መሪ መልዕክት ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል። በቆይታውም:-
👉 የኢፌዴሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አፈጻጸሞች፣
👉 የክልል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች ተሞክሮ እና ምክረ ሃሳብም ይቀርባል።
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ባለ ድርሻ አካላት የትብብር መድረክ አፈጻጸምም እንደሚገመገም እና ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።
ዘጋቢ፦ ዋሴ ባዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን