“ለመትከል ያቀድነው ዕቅድ ከታሰበው በላይ ተሳክቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

29

ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ተዓምር እንደሚሠሩ ዛሬ ዳግም ታይቷል ብለዋል።

“በመትከል ማንሠራራት” በሚል መሪ መልዕክት በአንድ ቀን 700 ሚልዮን ዛፎችን ለመትከል ያቀድነው ዕቅድ ከታሰበው በላይ ተሳክቷል ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አመራሮች እና ሠራተኞች፣ የግልና የመንግሥት ተቋማት፣ ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሕጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ አረጋውያን፣ ወንዶች እና ሴቶች ለአረንጓዴ አሻራ፣ ዛሬ በማለዳ ከወፎች ቀድመው ወጥተዋል።

አረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያውያን ባሕል እየኾነ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን መልክም እየቀየረ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያን ታሪክም እየቀየረ ነው። የዓለምንም መልክ እየቀየረ ነው።

ይሄንን ተልዕኮ የሚያስተባብሩትን፣ ጥሪያችንን ሰምተው ወጥተው የተከሉትን ሁሉ እናመሰግናለን። ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ዜጎች በብዛት እና በምልዐት ስላደረጉት ተሳትፎ በኢትዮጵያ ስም እናመሰግናለን።

መትከል ለልጆቻችን ጥላ መዘርጋት ነው!

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ83 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው የመሠረተ ልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።
Next articleየማኅበረሰቡን ጤና ለማሻሻል መከላከልን መሠረት ያደረገ የዘገባ ሽፋን መሥጠት ይገባል።