
ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ከሁነት መከታታያ ማዕከል ኾነው መረጃዎችን አጋርተዋል። በመረጃቸው ኢትዮጵያውያን የመሪያቸውን ጥሪ አክብረው ችግኝ የመትከል ሂደታቸውን ቀጥለዋል ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የመሪያቸውን ጥሪ ተከትለው ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ሲሰጡ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም ያሉት ሚኒስትር ድኤታው የመሪን ጥሪ ሰምተው፣ ዘምተው ሀገራገቸውን አቅንተዋል፣ አጽነተዋል ነው ያሉት።
የመሪን ጥሪ ተቀብለው ደማቸውን ገብረው ነጻነታቸውን ማጽነታቸውንም ገልጸዋል። ሀገርን ሲያቆሙ መኖራቸውንም ተናግረዋል። በቅርብ ዓመታት በልማቱ በነበራቸው የሀገራቸው ጥሪ ከዕለት ጉርሳቸው ቀንሰው ለሕዳሴ ግድብ አዋጥተው ታላቅ ፕሮጀክቶች መሥራታቸውን ተናግረዋል።
ዛሬም በሌላ ምዕራፍ ኢትዮጵያውያን ለመሪያቸው ጥሪ ምላሽ የሚሰጡበት ዕለት ነው ብለዋል።
እስከ ቀን 9:00 ሰዓት 648 ነጥብ 4 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ገልጸዋል። ይህም የቅዱን 93 በመቶ ነው። 27 ሚሊዮን በላይ ወገኖች መሳተፋቸውንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እና ትጋት ለትውልድ አሻራቸውን እያሰፉ መኾናቸውን ገልጸዋል። እያደረጉት ላለው ሁሉ መንግሥት ምስጋና ማቅረቡን አንስተዋል። የታሰበው እንደሚሳካም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!