
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ የኢትዮጵያ መሪዎቿ እና ሕዝቦቿ ከዳር እስከ ዳር አጀንዳቸው እና ተግባራቸው አንድ እና ያው ነው – በአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያን አረንጓዴ ማልበስ። ከፍተኛ መሪዎች በየአካባቢው ስምሪት ወስደው እና ሕዝብን እያስተባበሩ አረንጓዴ አሻራቸውን እያሳረፉ ይገኛሉ።
የትምህርት ሚኒሦትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያ ለልጆቻችን፣ ለልጅ ልጆቻቸን እና ቀጥሎም ለሚመጣው ትውልድ ምቹ መኖሪያ እንድትኾን ኀላፊነት አለብን ብለዋል። የወደፊቱን ትውልድ በዕውቀት መቅረጽ ብቻ ሳይኾን የተቃጠለ ዓለም እንዳይወርስ ምቹ አካባቢንም ለማስረከብ በጋራ መሥራትት አለብን ነው ያሉት።
አረንጓዴ አሻራ ለሁሉም የሰው ልጆች አጀንዳ እና ኀላፊነት ስለመኾኑም ተናግረዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ። ችግኝ የሚተከለው ለየትኛውም የፖለቲካ ውግንና ወይም ቡድን ተብሎ ሳይኾን ሰው መኾንን እና ሰው ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ግንኙነት በመረደት ሊኾን ይገባልም ብለዋል። ችግኝ መትከል ትልቅ ሀገራዊ ቁም ነገር ነው፤ ለልጆች ትምህርት እና ዕውቀት ከመስጠት እኩል፣ ስለምናወርሳቸውን አረንጓዴ ሀገር እና ምቹ ዓለም መሥራት አለብን ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን