በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ እየተካሄደ ነው።

26

የወረዳዉ ዋና አሥተዳዳሪ ሳሙኤል መርሻ እንደወረዳ በ19 ቀበሌዎች የተከላ ሳይቶች ተለይተው ችግኝ ተከላ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዘበነ እሸቱ በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች ችግኞች ይተከላሉ፤ ጸድቀው ለጥቅም እንዲደርሱም እንክብካቤ ይደረጋል ብለዋል።

በችግኝ ተከላው የመንግሥት ሠራተኞች፣ የሃይማኖት አባቶችና ኅብረተሰቡ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮችና አባላት ተሳትፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አረንጓዴ አሻራ ለሀገራዊ ልማት በጋራ የመቆም ባሕልን ያጎለበተ ነው” የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ
Next article“ለትውልድ ስለምናወርሰው አረንጓዴ ሀገር እና ምቹ ዓለም መሥራት አለብን” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ