
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በመላ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አሻራቸውን ያሳረፉት የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ.ር) የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ትርጉሙ ብዙ ነው፣ ከአካባቢ ጥበቃም ያልፋል ነው ያሉት።
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የተረጋጋ እና ሰላማዊ አከባበር እንዲኖር ለማድረግ፣ በተፈጥሮ መዛባት የሚመጡ አደጋዎችን ለመከላከል ሰፊ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት።
ባለፉት ዓመታት ታሪክ መሠራቱንም ገልጸዋል። ዛሬ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የዜግነት ግዴታ ያለብን በመኾኑ በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኝ ተክለን ታሪክ የምንሠራበት ነው ብለዋል።
የአረንጓዴ አሻራ ለመጭው ትውልድም ጥሩ መደላድል የሚፈጠርበት መኾኑንም ነው የተናገሩት።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን