
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ከሁነት መከታታያ ማዕከል ኾነው መረጃዎችን አጋርተዋል። ባጋሩት መረጃም በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፉ መኾናቸውን ገልጸዋል።
እስከ ቀኑ 7:00 ድረስ 517 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውንም ገልጸዋል። ይህም የዕቅዱ 74 በመቶ ነው ብለዋል። ተጨማሪ ተከላዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
እስከ 7:00 ድረስ 21 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሰዎች መሳተፋቸውንም ተናግረዋል። ይህም ኢትዮጵያውያን የመሪያቸውን ጥሪ ተቀብለው በራሳቸው ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል እየሠሩ ስለመኾናቸው ማሳያ ነው ብለዋል።
ችግኞችን የምንተክለው ለሀገር ደኅንነት እና የትውልድን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን