በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፡፡

143

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5 ሺህ 500 የላቦራቶሪ ምርመራ በ129 ሰዎች የኮሮናቫይረስ መገኘቱን ጤና ሚኒስቴር ገልጧል፡፡

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 934 ደርሷል፡፡

ጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው ከኮሮናቫይረስ ጋር በተገናኘ የአንድ የ80 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ህይወት አልፏል። ሟቿ ወደ ሆስፒታል ለሌላ ህክምና በመጡ በአንድ ሰዓት ወስጥ ህይወታቸው ማለፉን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡ በአስክሬን ምርመራም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 20 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ከአንድ እስከ 90 ዓመት የሆናቸው 75 ወንዶችና 54 ሴቶች ናቸው፡፡ ከአነዚህ ውስጥ 124 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ የደቡብ አፍሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ የአሜሪካ፣ የኤርትራ እና የሱዳን ዜጎች ናቸው፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 101 ከአዲስ አበባ፣ 10 ከአማራ፣ ስድስት ከሶማሌ፣ አምስት ከትግራይ፣ አምስት ከኦሮሚያ፣ አንድ ከሃረሪ እና አንድ ከጋምቤላ ክልሎች ነው፡፡

በሌላ በኩል ትናንት 19 ሰዎች (2 ከትግራይ ክልል፣ 6 ከአፋር ክልል፣ 1 ከሶማሌ ክልል እና 10 ከአዲስ አበባ) ከበሽታው አገግመዋል፤ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 281 ደርሷል፡፡

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መግባቱ ከተረጋገጠበት ዕለት እስከ ዛሬ 136 ሺህ 868 የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ1ሺህ 934 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር መረጃ መላክታል፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥ የተደረጉ የላቦራቶሪ ምርመራ ናሙናዎቹ ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉት ተወስዶ የተከናወነ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleበኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፡፡
Next articleአዲሱ የሞባይል ሰብስቴሽን ሥራ መጀመርም በኃይል እጥረት ምክንያት የቀዘቀዘውን የደብረ ታቦር ከተማ ምጣኔ ሀብት እንደሚነቃቃው ተመላከተ፡፡