
ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር መሠረታዊ ጥያቄያችንን የሚመልስ እና ከሀገር አልፈን ለዓለም የምንተርፍበት ንቅናቄ ነው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገልጸዋል፡፡
አቶ አደም ፋራህ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በጅግጅጋ ከተማ ችግኝ ተክለዋል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድን ነው ብለዋል፡፡
በየዓመቱ የራሳችንን ሪከርድ ያሻሻልንበት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ ከሌሎች ሳንጠብቅ በራስ ተነሳሽነት ምሳሌ የኾንበት ነው ያሉት አቶ አደም ፋራህ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሁሉም በንቃት እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!