
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በመላ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው።
በአዲስ አበባ ዘነበወርቅ አካባቢ የአረንጓዴ አሻራቸውን ያሳረፉት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ ( ዶ.ር) ለነገዋ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራችን በማሳረፋችን ደስተኞች ነን ብለዋል።
ለኢትዮጵያ መንሠራራት ሁሉም እንዲተክል ጥሪ አቅርበዋል። የአረንጓዴ አሻራ ለኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ነው፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዲሠራራ እያደረገ ነው፣ ተረጅነት እንዲወገድ፣ የምግብ ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ፣ ሌማት እንዲሞላ እያደረ ነው ብለዋል።
የአረንጓዴ አሻራ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መፍጠር መኾኑን ተናግረዋል። ንጹሕ አየር መፍጠር፣ የእያንዳንዱን ቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የፖለቲካ ሥራ አለመኾኑን ገልጸዋል።
የአንድ ሀገር የተረጋጋ ኢኮኖሚ የመፍጠር ሂደት የፖለቲካ ሥራ አለመኾኑም አንስተዋል። ሁሉም ሰው በየአካባቢው ችግኝ ሲተክል ለራሱ መኾኑን ነው ያመላከቱት። የአረንጓዴ አሻራ የዜጎችን ጥቅም ማረጋገጫ መኾኑንም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን