
ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ችግኝ መትከል መድኃኒት መትከል ነው፤ ምግብ መትከል ነው ብለዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአፈርና ውኃ ጥበቃን እንደሚያስተካከልም ገልጸዋል። ክልሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚገኘበት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በዚህ ሥፍራ ችግኝ መትከል የተለየ ትርጉም አለው ነው ያሉት።
የክልሉ ነዋሪዎች ከጠዋቱ ጀምረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እያካሄዱ መኾናቸውን ገልጸዋል። ይህ የታሪክ እጥፋት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የተጀመረው ጥረት እንዲሳካ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ችግኞች እየተተከሉ መኾናቸውን ገልጸዋል። ችግኝ ከመትከል ባሻገር መንከባከብ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል። ሁሉም የተከለውን እንዲንከባከብ ጥሪ አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!