
አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ.ር)ን ጨምሮ የሥራ ኀላፊዎች እና ሠራተኞች በአዲስ አበባ አይ ሲቲ ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በዚህ መርሐ ግብር መልእክት ያስተላለፉት ሚኒስትሩ ሀገሪቱን በአረንጓዴ ልማት ለማልበስ እንደዚህ አይነት መነቃቃቶች እና መርሐ ግብሮች ወሳኝ ናቸው ብለዋል።
ሥነ ምህዳርን ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ መሥራት ለማይበገር የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ በመኾኑ ሚኒሥቴር መሥሪያ ቤቱም ለዚህ ስኬት በትኩረት ይሠራል ብለዋል።
የሚኒስቴሩ ሠራተኞች በመርሐ ግብሩ በመሳተፍ አሻራቸውን በማሳረፉቸው ደስ ስለመሰኘታቸውና ተንከባክበውም ዛፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ስለመኾናቸው ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ አዲሱ ዳዊት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን