ከ4 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ የጥምር ደን ችግኞች ይተከላሉ።

16

ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዚህ ዓመትም አጠቃላይ ለመትከል ከታቀደው ችግኝ ውስጥ ከ4 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ የሚኾነው የጥምር ደን ችግኞች መኾናቸውን በግብርና ሚኒሰቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ፋኖስ መኮንን ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥም ከ632 ሚሊዮን በላይ የሚኾኑት የፍራፍሬ ችግኞች ናቸው ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ከመትከል ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት እና የሥራ እድል ከመፍጠር አኳያ ፋይዳው የጎላ ነው።

ከዚህ በፊት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተተከሉ ችግኞች አሁን ላይ ለምግብነት እና ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘታቸውን ገልጸዋል። ተጨማሪ የምግብ ዓይነቶችን እና የእንስሳት መኖ ማግኘት መቻሉንም ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት በአፈር እና ውኃ ጥበቃ በተሠራባቸው አካባቢዎች በተሠራው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እና የሥነ አካላዊ ሥራ 33 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም ተደርጓል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እየተካሄደ ነው።
Next article“ሥነ ምህዳርን ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ መሥራት ለማይበገር የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ነው” በለጠ ሞላ (ዶ.ር)