በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እየተካሄደ ነው።

7

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ይነሳ ሦስቱ ቀበሌ የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ከንጋት ጀምሮ እየተካሄደ ነው።

በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላው ላይ የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሰፋ ጥላሁን እና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ማስተዋል አሰሙን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተው ከሕዝቡ ጋር በመኾን አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

በተከላው የዞን እና የወረዳ መሪዎች እንዲሁም የቀበሌው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ተመስገን ደግአረገ በ13 ቀበሌዎች ችግኞች እንደሚተከሉ እና የተተከሉ ችግኞችን ለማጽደቅ ታልሞ እንደሚሠራ ተናግረዋል።

የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኀላፊ በለጠ ጥጋቡ የሚተከሉ ችግኞችን በእንክብካቤ የማሳደግን ጉዳይ አደራ ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ዋሴ ባዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበአሚኮ ሰቆጣ ኤፍ ኤም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
Next articleከ4 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ የጥምር ደን ችግኞች ይተከላሉ።