
ሰቆጣ፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን ሰቆጣ ኤፍ ኤም ቅርንጫፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በተከላ መርሐ ግብሩም የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ገቢዎች መምሪያ ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
አሚኮን በሚያክል ትልቅ ሚዲያ ላይ አሻራቸውን በታሪካዊ ቀን እና በታሪካዊ ቦታ በማስቀመጣቸው መደሰታቸውን የገቢዎች መምሪያ ኀላፊ አበባው ከሆነ ተናግረዋል።
አሚኮ ከተዓማኒ የመረጃ ምንጭነቱ ባሻገር በልማቱ ዘርፍም ቀዳሚ ነው ያሉት አቶ አበባው ለዚህም ማሳያው በሰቆጣ ከተማ ያሥገነባው የሚዲያ ተቋም ነው ብለዋል።
የተከሉትን ችግኝም እንደሚከታተሉት ጠቁመዋል።
በሰቆጣ ኤፍ ኤም ቅርንጫፍ ተገኝተው አሻራቸውን ያስቀመጡት የገቢዎች መምሪያ ሠራተኛ ኃይሌ አምሳሉ የተተከሉ ችግኞችን የገቢዎች መምሪያ ሠራተኞች ለመንከባከብ ዝግጁ ናቸው ብለዋል።
አሚኮ ከዘገባ ሽፋን ባሻገር አረንጓዴ አሻራን የሚተገብር ተቋም መኾኑን በተግባር ስለማየታቸው ነው የተናገሩት።
የሰቆጣ ኤፍ ኤምን ውብ እና ማራኪ ለማድረግ የተተከሉ ችግኞችን እንደሚንከባከቡ የተናገሩት ደግሞ የተቋሙ ሠራተኛ አማረ ሰለፍ ናቸው።
ዘጋቢ ፦ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን