ለደብረ ታቦር ከተማ ተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ የሞባይል ሰብስቴሽን ሥራ ጀመረ።

168

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2012 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ፣ የፌዴራልና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች 50 ሜጋ ዋት የሚያመነጨውን የሞባይል ሰብስቴሽን ሥራ አስጀምረዋል።

በደብረ ታቦር ከተማ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ምክንያት ሥራ ያቆሙና በፈረቃ የሚጠቀሙ እንደነበረ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ተጨማሪ የሞባይል ሰብስቴሽን ግንባታውም የከተማዋን ነዋሪዎችና ኢንዱስትሪዎችን ጥያቄ መመለስ እንደሚችል ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ኃላፊ አቶ ውበት አቤ ከዚህ በፊት ደብረታቦር፣ ወረታ፣ አዲስ ዘመንና ሌሎች ከተሞች 14 ነጥብ4 ሜጋ ዋትኤሌክትሪክ ኃይል ይጠቀሙ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ የሕዝቡን የመልማት ፍላጎት ለማሟላት አዲስ የሞባይል ሰብስቴሽን ዛሬ ሥራ እንዲጀምር መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

አዲሱ ተጨማሪ የሞባይል ሰብስቴሽን 50 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ መሆኑንም አቶ ውበት አስታውቀዋል። ተጨማሪ የኃይል አቅርቦቱ ብዙ የመልማት አማራጮችን የሚስብ በቂ ኃይል መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ግርማ ተጫነ-ከደብረ ታቦር

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleየኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሕዝቡን የመልማት ጥያቄ የሚመልሱ እንዲሆኑ ርእሰ መሥተዳደሩ አሳሰቡ።
Next articleየሚኒስትሮች ምክር ቤት በ2013 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥተ ረቂቅ በጀት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡