“እስከ ረፋዱ 5:00 ሰዓት 355 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል” የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

20

ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ የ2017 ዓ.ም የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሂደትን እስመልክተው ከሁነት መከታተያ ሩም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 700 ሚሊዮን ቸግኞችን የመትከል እቅድ ለማሳካት እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል።

እስከ ረፋዱ 5:00 ሰዓትም 355 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል። 14 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዜጎች በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ መሳተፋቸውንም ገልጸዋል።

በተከላ ሂደቱ የተሳተፉ ዜጎችንም አመሥግነዋል። ዕቅዱን ለማሳካት የተከላ ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleደሴን ከጎርፍ ተጋላጭነት ለመጠበቅ ችግኞችን መትከል ይገባል።
Next articleየተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ ከኅብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ገለጸ።