ደሴን ከጎርፍ ተጋላጭነት ለመጠበቅ ችግኞችን መትከል ይገባል።

10

ደሴ፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሐግብር አካል የኾነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በደሴ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ ላይ የደሴ ከተማ እና የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች እንዲኹም በየደረጃው ያሉ የተለያዩ የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፎ እያደረጉ ነው።

ከአሚኮ ጋር ቆይታ የነበራቸው የከተማዋ ነዋሪዎችም ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር መሳተፋቸውን ገልጸው ዘንድሮም የተከሏቸውን ችግኞች እንደሚንከባከቡ ገልጸዋል።

በተፈጥሮ አቀማመጧ ለጎርፍ ተጋላጭ የኾነችው ደሴ ከተማን ከተፈጥሮ አደጋ መከላከል የሚቻለው ችግኞችን በመትከል ተንከባክቦ ማጽደቅ ሲቻል እንደኾነ ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት።

የደሴ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ እዩኤል ሙልዬ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደ ቡና አፕል እና ሌሎችም ፍራፍሬዎች እንደተተከሉ ተናግረዋል።

የከተማ እና የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎችን በማስተባበር የአካባቢ ሥነምህዳርን ለማስጠበቅ በትኩረት ይሠራልም ነው ያሉት ኀላፊው።

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም እና ምርታማነትን ለመጨመር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የማይተካ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

አቶ እዩኤል የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ሀገር አቀፍ መርሐግብሩን ጨምሮ በቀጣይ ቀናት የከተማዋን ሥነ ምህዳር ያማከሉ የተለያዩ ችግኞች በትኩረት ይተከላሉም ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ሰልሀዲን ሰይድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleችግኞችን በመትከል የመጽደቅ ምጣኔያቸውን ማሳደግ ይገባል።
Next article“እስከ ረፋዱ 5:00 ሰዓት 355 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል” የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት