
በካራማራ ሰንሰለታማ ተራሮች በተከበብችው ጅግጅጋ ከተማ አረንጓዴ አሻራ ተጨማሪ ሃብቷ እና ውበቷ ነው።
የምስራቅ ኢትዮጵያ ጌጥ፣ የብዙኃን መናህሪያ እና የእንግዳ ተቀባይ ሕዝብ ምድር በሆነችው ጅግጅጋ ከተማ ዛሬ የአረንጓዴ አሻራችንን አሳርፈናል።
ዛሬ በኢትዮጵያ “በመትከል ማንሰራራት” በ7ኛ ዓመት 700 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር እየተተከሉ ነው። በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ እስከ 2018 ዓ.ም. 50 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።ይህ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም በዓለም ላይ ትልቁ የአረንጓዴ ልማት ትግበራ ነው።
በበተባበሩ ክንዶች በመደመር የከበረ እሳቤ መሥራት በዓለም ፊት ሁሉ አንደኛ የመሆን ቀጥተኛው ጎዳና ለመሆኑ አረንጓዴ ዐሻራችን የሚታይ የሚጨበጥ ምስክር ነው።
የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ በዚህ ሃገራዊ የልማት ሰልፍ ላይ ናቸው። ከእቅዳችን ውስጥ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ 46 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል።
በጅግጅጋም ሆነ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች የምናደርገው የአረንጓዴ ዐሻራ የሃገራዊ ተግባሩ ተደማሪ፣ ከአካባቢው ውበት የሚሻገር በኢኮኖሚ የሚመነዘር፤ ከነባራዊ የኑሮ መሰረት እና ኃብት ከሆኑ እሴቶችም ጋር ሰም እና ፈትል ሆኖ የሚስማማ የታሪክ ማህተማችን ነው።