የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሕዝቡን የመልማት ጥያቄ የሚመልሱ እንዲሆኑ ርእሰ መሥተዳደሩ አሳሰቡ።

147

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2012 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ያሉ የኢንቨስትመንት ቦታዎችን ዛሬ ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በከተማው ያሉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ወደ ሥራ በመግባት ረገድ ውስንነት እንዳለባቸው ገልጸዋል። በዚህ ምክንያት የገበያ እና የሥራ ዕድል ባለመፍጠር ሕዝቡን ለምሬት እንዳይዳርጉ ፈጥነው እንዲጠናቀቁ ድጋፍና ክትትል መስጠት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

የኢንስትመንት ፕሮጀክቶች የሕዝቡን የመልማት ጥያቄ የሚመልሱ እንዲሆኑም ትኩረት አድርጎ መሥራት እንደሚያስፈልግ ርእሰ መሥተዳድሩ አስገንዝበዋል።

ኃላፊዎቹ በ6 ቢሊዮን ብር እየተገነባ 30 በመቶ የደረሰውን የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ጎብኝተዋል። የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ግንባታን የመሠረት ድንጋይም አስቀምጠዋል።

የዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ግንባታና ማስፋፊያ የልማት ሥራዎችን፣ የደብረታቦር የባህል ግንባታ ሂደትንና ጊዚያዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ (ሞባይል ሰብስቴሽን) እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።

የአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር አብርሃም በላይ (ዶክተር፣ ኢንጂነር)፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና ሌሎችም የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን ከርእሰ መሥተዳድሩ ጋር እየጎበኙ ናቸው፡፡

ዘጋቢ፦ ግርማ ተጫነ-ከደብረ ታቦር

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መልበስ መዘንጋት እንደሌለበት የዓለም ጤና ድርጅት አሳሰበ፡፡
Next articleለደብረ ታቦር ከተማ ተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ የሞባይል ሰብስቴሽን ሥራ ጀመረ።