
ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያውያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን በጀመሩ በ7ኛው ዓመት ዛሬ በአንድ ጀንበር ብቻ 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጀምሯል።
በአማራ ክልልም መሪዎች ከሕዝቡ ጋር በንቅናቄ በመውጣት በሁሉም አካባቢዎች የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ እያካሄዱ ይገኛሉ።
የክልሉ እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር መሪዎችም ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በመኾን ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በድባንቄ ተራራ ላይ ችግኝ እየተከሉ ነው።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!