“አረንጓዴ አሻራ የሕልውና ጉዳይ ነው” የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር

9

ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ የሥራ ኀላፊዎች በሶማሌ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ ተሳትፈዋል።

የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ ሙሐመድ በችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ሕዝቡ እየተሳተፈ መኾኑን ነው የገለጹት።

በተለይም ደግሞ በድርቅ ተጋላጭ የኾኑ እንደ ሶማሌ ክልል የመሳሰሉ ቆላማ አካባቢዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሕልውና ጉዳይ መኾኑን ገልጸዋል።

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚመጣ ችግርን ለመከላከል ማኅበረሰቡ ከአንድ ቀን ጀንበር ተከላ ባለፈ በማንኛውም ጊዜ ባለው ቦታ መትከል እንዳለበትም መክረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሕዝቡ ተፈጥሮን ወደ መንከባከብ ነባር ባሕሉ መመለስ መቻሉን ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።
Next article“አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ ያስቀመጠችውን ግብ ማሳካት እንደምትችል አንዱ ማሳያ ነው” የግብርና ሚኒስቴር ግርማ አመንቴ (ዶ.ር)