በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሕዝቡ ተፈጥሮን ወደ መንከባከብ ነባር ባሕሉ መመለስ መቻሉን ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።

9

ባሕርዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ባለፉት ሰባት ዓመታት በተከታታይ እንደ ሀገር እና እንደ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል ነው ያሉት።

በክልሉ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በርካታ ሕዝብ በተሳተፈበት እየተከናወነ መኾኑን ገልጸዋል። ከችግኝ ዝግጅት እስከ ጉድጓድ ቁፋሮ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውሰዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሕዝቡ ተፈጥሮን ወደ መንከባከብ ነባር ባሕሉ መመለስ መቻሉን ተናግረዋል።

በተለይም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በግብርና ልማት ውጤት እያስገኘ መኾኑን ገልጸዋል። ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።

የክልሉ ሕዝብ በችግኝ ተከላው ያሳየውን ተሳትፎ በችግኝ እንክብካቤውም በመድገም ችግኙ ለውጤት እንዲበቃ ጥረቱን ማጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ኢቢሲ እንደዘገበው በዚህም በየሁለት ሳምንቱ ችግኞችን ውኃ በማጠጣት፣ በመኮትኮትና ከንክኪ በመከለል ለውጤት ማብቃት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻ ልማት ላይ ችግኞችን መትከል የበለጠ ውበት እያላበሰ ነው።
Next article“አረንጓዴ አሻራ የሕልውና ጉዳይ ነው” የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር