“የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ ትልቁ ግባችን ነው” ርእሰ መሥተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ.ር)

9

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ታርጫ አካባቢ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ.ር) “ባለፉት ዓመታት የተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን አግኝተንበታል” ብለዋል።

የክልሉ ሕዝብ ለዘመናት ደኖችን ጠብቆ እንደቆየ አንስተዋል። ሕዝቡ የደን ጥበቃን ባሕል አድርጎ ይዞ ስለመጣ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሲመጣ እንግዳ እንዳልኾነ ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን መትከላቸው እና ተስፋ ሰጭ ውጤቶች እንደተገኙ ነው የተናገሩት።

የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል፣ የአካባቢ ውበትን የሚመልስ ሥራ ተሠርቷልም ነው ያሉት።

የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ እና የአፈር ጥበቃን በማስጠበቅ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ነውም ብለዋል።

ችግኝ መትከል ብቻ ሳይኾን ችግኞች ለተተከሉለት ዓላማ ደርሰዋል ወይ ለሚለው ትኩረት ማድረግ ይገባል ነው ያሉት።

“መትከል ቀዳሚው ሥራችን ነው፣ የተተከሉ ችግኞች መንከባከብ ደግሞ ትልቁ ግባችን ነው” ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በየዓመቱ የራሷን ክብረ ወሰን እየሻሻለች መቀጠሏን አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።
Next articleበአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻ ልማት ላይ ችግኞችን መትከል የበለጠ ውበት እያላበሰ ነው።