
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው። ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በጅግጅጋ ከተማ አሻራቸውን ማሳረፋቸውን ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው ያሉት አቶ አደም ሕዝቡ በሚገባ እየተረዳው መኾኑን ገልጸዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት አደጋዎችን ለመቋቋም፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ምርትና ማርታማነትን ለማሳደግ እንደሚረዳ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በየዓመቱ የራሷን ክብረ ወሰን እያሻሻለች መቀጠሏንም ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ያለውን ጫና ለመቋቋም ኢትዮጵያ ምሳሌ መኾን አለባት ብለን የጀመርነው ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን