ጠቅላላ ከተዘጋጁት ችግኞች 2 ነጥብ 9 ቢሊዮኑ ሀገር በቀል ዝርያዎች ናቸው።

11

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመረጃ ሁነት መከታተያ ክፍል ላይ እስካሁን የተተከሉ ችግኞችን በተመለከተ መግለጫ ተሰጥቷል።

የብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ የቴክኒክ ኮሚቴ ሠብሣቢ አደፍርስ ወርቁ (ዶ.ር) በዚህ ዓመት በ116 ሺህ የችግኝ ጣብያዎች 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ተፈልቷል።

ከዚህ ውስጥ 3 ነጥ 9 ቢሊዮኑ ከ100 በላይ ዝርያዎች የያዙ የደን ችግኞች፣ 4 ነጥብ 3 ቢሊዮን የጥምር ደን ችግኞች እና 632 ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል ነው ያሉት።

ጠቅላላ ከተዘጋጁት ችግኞች 2 ነጥብ 9 ቢሊዮኑ ሀገር በቀል ዝርያዎች እንደኾኑም ጠቁመዋል።

ከተዘጋጀው ችግኝ ውስጥ ደግሞ 4 ነጥብ 7 ቢሊዮኑ በላስቲክ የተዘጋጀ ችግኝ መኾኑን ገልጸዋል።

አጠቃላይ ለተከላ ከተዘጋጀው ውስጥ ደግሞ 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ እስከ ባለፈው አርብ መተከሉንም አብራርተዋል።

በአንድ ጀንበር ደግሞ 700 ሚሊዮን ችግኝ እንደ ሀገር ለመትከል መታቀዱን ገልጸዋል።

የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከመትከል ባሻገር ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር እና ክልሎች ተሞክሮ የሚለዋወጡበት መኾኑንም ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የሚተከሉት ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው” ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ
Next articleኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በየዓመቱ የራሷን ክብረ ወሰን እየሻሻለች መቀጠሏን አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።