
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርዕሰ መስተዳደሩ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ዕቅድ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል::
የችግኝ ተከላ ተግባር በአንድ ጀንበር በማካሄድ የሚያበቃ ባለመኾኑ ከዚህ በፊት የተተከሉትን መንከባከብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የመሬት መራቆት ብዝሃ ህይወትን ስጋት ላይ እንደሚጥል ጠቅሰው፣ አካባቢያችንን ለማስዋብና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እንዲኹም የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖን ለመቋቋም ችግኝ ተከላን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ የበኩላችንን በመወጣት ለነገ ትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋት እናስቀምጥ ሲሉ ርዕሰ መስተዳደሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን