
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ እየተካሄደ ነው።
የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ ሀገራዊ ንቅናቄው በአፋር ክልል እየተካሄደ መኾኑን ገልጸዋል። ችግኝ ትርጉሙ ከችግኝ በላይ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ዛሬ አሻራችን እያስቀመጥን ያለነው የምግብ ሉዓላዊነታችን ለማረጋገጥ፣ ለትውልድ ዕዳን ሳይኾን ክብር ለማስረከብ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከፍ ለማድረግ መኾኑን ገልጸዋል።
ባለፉት ዓመታት እንደ ሀገር በተሠሩ ሥራዎች ክብር ተጎናጽፈናል፣ ተከብረናል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ ትታወቅበት ከነበረው ግጭት እና ረሃብ እየወጣች የኢትዮጵያ እና የኢትጵያዊነት ልክ ለዓለም እየተገለጠ መኾኑን ገልጸዋል።
ካሰብን፣ ከወሰን፣ በገባነው ቃል መሠረት መሬት ላይ ማሳረፍ እንደምንችል፣ እንደ ምንለወጥ፣ ለዓለም ተምሳሌት መኾን እንደምንችል ያሰያንበት ነው ብለዋል። ዛሬም በዓለም ታሪክ አዲስ ክብረ ወሰን ለማስመዝገብ እየሠራን ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ባለፉት ዓመታት ባገኘናቸው ውጤቶች ሳንዘናጋ፣ ኢትዮጵያን ከፍ የማድረግ ሥራ እንሠራለን ነው ያሉት።
የዛሬው ችግኝ ትርጉሙ ከችግኝ በላይ ነው፣ ምክንያቱም የነገ ትውልድ የሚኮራበት አሻራ ነው እያሠረፈን ያለነው፣ ዛሬ እየተከልን ያለነው የሀገር ክብር ባንዲራን ነው፣ ከፍ አድርገን እያውለበለብን ነው ብለዋል
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን