
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2012 ዓ.ም (አብመድ) የቀድሞው የቅርጫት ኳስ ዝነኛ ተጨዋች ማይክል ጆርዳን ዘረኝነትን ለመዋጋት የሚደረገው ትግል ለማገዝ 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድቧል፡፡
ዘርኝነትን በመታገል እኩልነትና ማኅበራዊ ፍትሕ እንዲሰፍን ለሚታገሉ ቡድኖች የገንዘብ ድጋፉን እንደሚያደረግም ታውቋል፡፡
ሐሳቡ የመጣው ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በነጭ የአሜሪካ ፖሊስ አንገቱን ተረግጦ መገደሉ ዓማቀፍ ውግዘትና ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ነው፡፡
የጆርዳን ብራንድ ፕሬዝዳንት ክሬግ ዊሊያምስ ‘‘ማይክል ጆርዳን እና ጆርዳን ብራንድ በቀጣይ 10 ዓመት 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመመደብ ከማኅበረሰቡ፣ ከሲቪል ማኅበራትና መንግሥት ጋር ሆነን በመሥራት ለውጥ ለመፍጠር እንሠራለን’’ ብለዋል፡፡
በጥቁሮች ዘንድ ያለውን የዘር መድሎ ለመለወጥ ብዙ መሥራት እንደሚቀርም ነው ፕሬዝዳንቱ ያመለከቱት፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ
በኪሩቤል ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡