
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ከሁነት መከታተያ ሩም በቀጥታ በሰጡት መረጃ የ2017 የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች እየተካሄደ ነው።
በ2017 ዓ.ም በአንድ ጀንበር መርሐ ግብር 700 ሚሊዮን ችግኝ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ መልዕክት እየተካሄደ ይገኛል። እስከ አሁን ጧት 3:00 ሰዓት 103 ሚሊዮን ችግኞች መትከል መቻሉን ገልጸዋል። 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሕዝብም በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ተሳትፏል ብለዋል።
እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ የታቀደውን ለማሳካት ይሰራል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን