
ባሕርዳር ፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጅባ ከተማ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ማለዳ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አስጀምረናል። ለሰባተኛው አመት ግባችን 700 ሚሊዮን ችግኞች ነው። በጋራ እናሳካው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን