“በጋራ እናሳከዋለን” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

11

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ ግንፍሌ አካባቢ ችግኝ ተክለዋል።

በችግኝ ተከላው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ዓመታት በተከልናቸው ችግኞች ታላቅ ገድል ሠርተናል ነው ያሉት።

በዓለም ላይ የሚያስገርም ድንቅ ተግባር መከናወኑን የተናገሩት ከንቲባዋ በ2017 ዓ.ም እየተደገመ መኾኑንም ገልጸዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድነት መያዙንም ተናግረዋል። ያለ ልዩነት የተተከለው ችግኝ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የማይበገር እንዲኾን ጽኑ መሠረት ጥሏል ነው ያሉት። ችግኝ በመትከል የምግብ ሉዓላዊነታችንን እናረጋግጣለን፣ የምንተክለው ምግባችንን ነው ብለዋል።

ጤናችንን ለመጠበቅ እንዲያስችለን እየተክልን ነው፣ የአየር ንብረት ለውጥን ነው እየተከላከልን ያለነው ነው ያሉት።

በአዲስ አበባ በሁሉም የችግኝ መትከያ ሥፍራዎች የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። ምቹ ከተማን ለመገንባት የተሳካ ሥራ እየተሠራ እንደኾነም ነው የተናገሩት።

“የአንድ ጀንበር ዕቅዳችንን ሳናሳካ አንገባም፣ ሁልጊዜ ከዕቅድ በላይ ነው የምናሳካው፣ በጋራ እንትከል፣ ሁሉም በተባበረ ክንድ ችግኞችን እንትከል፣ በጋራ ስንተክል ፍቅርን፣ መልካም ሃሳብን ነው የምንተክለው፣ ለልጆቻችን የሚተላለፍ አሻራ ነው የምንተክለው፣ በጋራ እናሳከዋለን እንበርታ” ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበምዕራብ ጎንደር ዞን የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተጀምሯል።
Next articleየ2017 ዓ.ም የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ መልዕክት፦