
ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የአራተኛ ቀን ውሎ እያካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ በአራተኛ ቀን ውሎው የክልሉን መንግሥት ጥቅል በጀት መርምሮ አጽድቋል።
በዚህም መሠረት የአማራ ክልል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ጥቅል በጀት 225 ቢሊዮን 453 ሚሊዮን 779 ሺህ 237 ብር ኾኖ ጸድቋል።
የበጀት ድልድሉ የወጭ ፍላጎትን እና ተጨባጭ ሙያዊ አስተያየቶችን ተጠቅሞ የቢሮዎችን፣ የወረዳዎች እና የከተማ አሥተዳደሮችን ድርሻ ክፍፍል በመወሰን በአሥተዳደር እርከኖች መካከል የሚጠበቀው ፍትሕዊነት እንዲኖር ታሳቢ ያደረገ መኾኑ ተገልጿል።
የሕዝብ አንገብጋቢ ችግሮችን ታሳቢ ያደረግ የካፒታል በጀት ድልድል መደረጉም ተመላክቷል።
የድህነት ተኮር ሴክተሮች የበጀት ድርሻቸው የተሻለ እንዲኾን የዓለም አቀፍ ስምምነቶችን እና ሀገራዊ አቅጣጫዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የበጀት ድልድሉ የተሠራ መኾኑ ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!