ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት ለመንግሥት ሥራዎች ማስፈፀሚያ የታወጀ ተጨማሪ በጀት አዋጅን አጸደቀ።

26

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ የአራተኛ ቀን ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በውሎው የ2017 በጀት ዓመት ለመንግሥት ሥራዎች ማስፈፀሚያ የታወጀ ተጨማሪ በጀት አዋጅን አጽድቋል።

የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን መሐሪ (ዶ.ር) ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት ለመንግሥት ሥራዎች ማስፈፀሚያ የታወጀ ተጨማሪ በጀት አዋጅን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ከመንግሥት ግምጃ ቤት፣ ለሀገራዊ ደሞዝ ጭማሪ፣ ከፌዴራል መንግሥት ተጠይቆ የተፈቀደ ብድር፣ በ2016 በጀት ዓመት ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ከገቢ ዕቅድ በላይ የተሠበሠበ መደበኛ ገቢ፣ ከውስጥ ገቢ፣ ከግብርና ምርምር ተቋማት በ2017 በጀት ከተፈቀደው በላይ የሠበሠቡት ገቢ ጠቅላላ 13 ቢሊዮን 758 ሚሊዮን 996 ሺህ 301 ብር ጥቅም ላይ መዋሉን ገልጸዋል።

የ2017 በጀት ዓመት በጀትን ለማወጅ እና የበጀቱን አሥተዳደር ለመወሰን በወጣው አዋጅ የተሠጠው ሥልጣን በዚህ አዋጅም ተፈጻሚ ይኾናል ነው ያሉት።

የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ ሃናን አብዱ የቋሚ ኮሚቴውን የውሳኔ ሃሳብ አቅርበዋል።

በውሳኔ ሃሳባቸውም የቀረበው ተጨማሪ በጀት የክልሉ መንግሥት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ተቀባይነት ባለው መልኩ ለመንግሥት ሥራዎች በሥራ ላይ የዋለው እና ሕጉን ተከትሎ የተፈጸመ በመኾኑን ቋሚ ኮሚቴው በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“አሚኮ ለሀገር አንድነት ተጨማሪ አቅም ኾኗል” ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ
Next articleደኖችን ስለመጠበቅ ሕጉ ምን ይላል?