ሀገራት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋጥ ትኩረት ሰጥተው መሥራት ይገባቸዋል።

13

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ጣሊያን በጋራ በመኾን ባዘጋጁት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጉባኤው በአፍሪካ ሲካሔድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፤ ይህም ሀገራት ለዘርፉ ትኩረት እንዲሰጡ ለማድረግም ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

የምግብ ሥርዓት ችግር እስካኹን 40 በመቶ የዓለም ሕዝብ ችግር ስለመኾኑም ጠቅላይ ሚኒስትሯ አንስተዋል።

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የዓለም የምግብ ሥርዓት እንዳይረጋጋ አድርጓል፤ ለከፍተኛ የዋጋ ንብረትም አጋልጧል ብለዋል። በአሁኑ ጊዜም ይህ የዋጋ ንረት በታዳጊ ሀገራት በአማካይ 30 በመቶ እንዲደርስ አስተዋፅኦ አድርጓል ነው ያሉት።

የዓለም የምግብ ሥርዓት ችግር አንዲረጋጋ ሰላም እና መረጋጋት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል። ችግር ውስጥ ያለውን ሕዝብ በምግብ ሥርዓት ውስጥ ቅድሚያ መሥጠት እና ማገዝ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ሥርዓታቸውን ለመቀየር እየወሰዱት ያሉት ርምጃ የሚደገፍ ነውም ብለዋል።

የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የሁሉም ግብ መሆን የሚገባው ጉዳይ ስለመኾኑም ጠቅላይ ሚኒስትሯ አስምረውበታል። በልቶ ማደርን ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱ ቤተሰብ በቂ እና ተመጣጣኝ ምግብ የሚያገኝበት ሥርዓትን መገንባት ማለት እንደኾነም ገልጸዋል።

የምግብ ሥርዓት ሲረጋጋጥ በራስ መተማመንን ያሳድጋል፤ ሁሉን አቀፍ መዳረሻችንንም ለማስተካከል ይረዳል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ።

ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ግባችን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የተመጣጠነ እና በቂ ምግብ እንዲያገኝ ማድረግ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“ጦርነት እና ግጭት በዓለም አቀፍ የምግብ ሥርዓት ግንባታ ላይ ትልቅ እንቅፋት ናቸው” አንቶኒዮ ጉተሬዝ