በድሬዳዋ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅ ላይ መረባረብ እንደሚገባ የአስተዳደሩ ከንቲባ አሳሰቡ፡

176

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 28/2012 ዓ.ም (አብመድ) በድሬዳዋ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ዛሬ ተጀምሯል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አሕመድ መሐመድ ችግኝ መትከልና አጽድቆ ለቁም ነገር ማድረስ ለሀገሪቱ በተለይ ለድሬዳዋ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ ኢዜአ ዘገባ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ፕሮግራም በድሬዳዋ አስተዳደር 1 ሚሊዮን500 ሺህ የፍራፍሬና የዛፍ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል፡፡

በድሬዳዋ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ የተፈጥሮ ሃብት መጠበቅና መንከባከብ ላይ መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፈው ክረምት ከተተከለው 719 ሺህ ችግኝ ወስጥ 82 በመቶ መጽደቁን በተደረገው ቅኝት መረጋገጡን ከንቲባ አሕመድ ገልጸዋል፡፡ ዘንድሮ የሚተከሉት ችግኞች በተሻለ ደረጃ እንዲጸድቁ መንከባከብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

Previous articleበሐረሪ ክልል በአረንጓዴ ልማት የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።
Next articleየግብዓት እጥረት እንዳጋጠማቸው አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡