ፀደይ ባንክ በቀጣይ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ተደራሽ ለመኾን እየሠራ ነው።

10

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፀደይ ባንክ ከማስተር ካርድ እና የሰፖርስ ኤዱኬሸን ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

የፀደይ ባንክ የዲጂታል እና ብራንች ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ታደሰ ባንኩ በዘርፉ ሥራ በጀመረባቸው ሦሥት ዓመታት በትልቅ አቅም የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ሥራ ላይ ነው ብለዋል።

ባንኩ ከሁለቱ ተቋማት ጋር ያደረገው የአብሮ የመሥራት ስምምነት የፀደይ ባንክ ደንበኞች አገልግሎትን በቀላል እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

በማስተርስ ካርድ ዓለማቀፍ የኾኑ አገልግሎቶችን ለደንበኞች ተደራሽ ለማድረግ እና በኮሚኒቲ ፓስ ተደራሽ ባልኾኑ አካባቢዎች ተደራሽ ለመኾን የሚያስችል እንደኾነም ጠቁመዋል።

ከሰፖርስ ኢዱኬሽን ጋር የሚደረገው ስምንነትም የተማሪዎች ክፍያን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እና ተማሪዎች የቁጠባ ባሕላቸው እንዲያድግ የሚረዳ ነው ብለዋል።

የማስተርስ ካርድ የቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ዳይሬክተር እልፍ አገድ ድርጅቱ ባንኮችን የሚያግዙ ከ300 በላይ ቴክኖሎጅ እንዳለው ነው የተናገሩት።

በቴክኖሎጂው ዘርፍም ከፀደይ ባንክ ጋር በመኾንም አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እንደሚሠሩም ገልጸዋል።

የትምህርት ቤት መረጃ አሥተዳደር ሥርዓትን እና የክፍያ አገልግሎቶችን በሰከላ ኤስ አይ ኤም ኤስ እንዲተገበር የሚያስችል ስምምነት መደረሱን የተናገሩት ደግሞ የሰፖርስ ኤዱኬሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ሙሉጌታ አሰፋ ናቸው።

ፀደይ ባንክ ወደ ሥራ በገባባቸው ሦሥት ዓመታት ከ630 በላይ ቅርጫፎች እና ከ12 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን በማፍራት ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማፍራቱ ተጠቅሷል።

ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡
Next article“የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሠራን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት