
አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የንግድ ባንክ ዲስትሪክት ሥራ አሥኪያጆች እና የባንኩ ባለሙያዎች በዋናው መሥሪያ ቤት እና በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።
ፕሬዝዳንቱ አቤ ሳኖ በዛሬው መርሐ ግብር 35 ችግኞች በዋናው መሥሪያ ቤት እና በቦሌ ለሚ ኢንዱሰትሪ ፓርክ ደግሞ 20 ሽህ ችግኞችን ተተክለዋል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ በመላ ሀገሪቱ በሁሉም የንግድ ባንክ ሠራተኞች ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታ ያላቸዉን ግማሽ ሚሊዮን ችግኞችን እንተክላለን ብለዋል።
ችግኝ መትከል የአየር ንብረት ለዉጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ሚናዉ የጎላ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዘዳንቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግና የተከሉ ችግኞችም ጸድቀዉ ለተፈለገዉ ዓላማ እስኪድረሱ መንከባከብ እንደሚገባ መክረዋል።
ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!